
የባለመብት ፖሊሲ
- ይህን ከክፍያ ነጻ የሆነ አፕ ከጉጉል ፕሌ በየነመረብ ሰልክ፣ ታብሌትና ዊንዶ 11 ፕሲ ላይ መጫን ይቻላል፡፡ የሶስት ሺህ ዓመት የዘመን መቁጠሪያ በቀላሉ ማየት ያስችላል፡፡ አፑን ከጫኑት በኋላ ኢንተርኔት ባይኖርም መጠቀም ይችላሉ፡፡
- ይህን አፕ ሲጠቀሙ ምንም አይነት የግል መረጃ ከእርሶ አይወስድም ወይንም ለሌላ ወገን አያስተላልፍም፡፡
- አፑ የሚያቀናብረውን የቀን መቁጠሪያ ውጤት በስልኮ ላይ ከማሳየት በሰትቀር በስልኮ መረጃ ቋት ላይ አያስቀምጥም ወይም ወደሌላ መገልገያ አያስተላልፍም፡፡
- አፑን በማንኛውም የዕድሜ ክልል ያለ ሰው መጠቀም ይችላል፡፡ የሚፈልጉትን ዓመት የዘመን ቀመር ከማሳየት ውጪ ሌላ ትልዕኮ የለውም፡፡
የአፑ አጠቃቀም
- አፑን ሲከፍቱ “English” እና “አማርኛ” የተጻፈበት መደብ ይታያል፤ የ”አማርኛው” ውይንም “English” ምደብ ሲጫኑ የ 12 ወር የወቅቱን ዓመት ቀን መቁጠሪያ ያገኛሉ፡፡
- እያንዳዱ የወር መደብ 10 ቦታ የተከፈለ ነው። የመጀመሪያ ክፍል ውስጥ የወሩ ስም፣ ዓመተምህረት፣ “-“፣ “+” መደቦች እና የአዲስ አበባን ሰዓት ያሳያል፡፡ “-”፣”+” መደቦች በመጫን ዓምቱን በአንዳንድ ዓምት በመጨመር ወይንም በመቀነስ የተለያየ ዓመት ቀን መቁጠሪያ ያገኛሉ፤ ወይንም ዓመተምህረቱ ላይ በመጫንና ዓመቱን በማጥፉት፤ በሚፈልጉት ዓመት በመተካት የቀን ምቁጠሪያውን ያገኛሉ።
- ማሳሰቢያ፦ የሚፈልጉትን ዓመት ከከተብ በኋላ ለማስኬድ የሚጫኑት “-”፣”+” ወይም ስልኮ ላይ ያለውን “Go” or return ኪ ነው፤ ይህ ሲሆን የጻፉት ዓምት በአንድ ዓመት ሊጨምር ወይንም ሊቀንስ ስለሚችል መልሰው “-” “+” በመጫን ማስተካከል ይችላሉ።
- አፑ የማይቀበላችውን ቁጥሮች ከከተቡ ወይንም ባዶ ከተው “reload/ ይጫኑኝ” መልዕክት ይመጣል መልክቱን ሲጫኑ አፑ እራሱን ያድሳል።
- የዛሬን ቀን ከሌሎቹ ቀናት ለመለየት በብርቱካናማ ቀይ በሆነ አራት መዓዘን ቅርጽ ውስጥ እዲታይ ተደርጓል። አፑ ላይ የሚታየው ሰዓት ዓመት ካልተቀያየረ በቋሚነት ይታያል።
- ”English” ሲጫኑ የኢትዮጵያንና የአውሮፓን ቀን መቁጠሪያዎች በአንድነት ተሰላስለውና ተጣምረው ይታያሉ። ከአንዱ አቆጣጠር የሌላኛውን አቻ ማግኘት በቀላሉ አስችሏል።
- የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የሚጀምረው ከመስከረም ሲሆን የአውሮፓኖቹ በታህሳስ መጨረሻ አካባቢ ነው፤ በዓመት፣ በወር ቀናትና በሰዓት አቆጣጠርም ልዩነቶች አሉ።
- ለምሳሌ የኢትዮጵያ ዓመት ከመስከረም አንድ እስክ ታህሳስ 22/23(Jan. 1 ) ባለው ግዜ ውስጥ በ 7 ዓምት ከዚህ ውጪ ከሆነ በ 8 ዓምት ከአውሮፓውያኑ ዓመት ያንሳል።
- በአንድ የአውሮፓውያ ወር ውስጥ ሁለት የኢትዮጵያ ተከታታይ ወሮች በክፊል በሮዝና በወርቃማ አረንጓዴ ቀለም ተለይተው ሲታዩ የአውሮፓኖቹ በነጭ ቀለም ተለይቷል።
- ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ለመቀየር መጀመሪያ ካሉበት ቀን መቁጠሪያ ላይ ሆነው ወሩንና ቀኑን (የፈረጁን) ያግኙ፤ ዓመተምህረቱ የተለየ ከሆነ አጥፍተው የሚፈለገውን ይክተብና ያስኪዱት (ማሳሰቢያውን አይርሱ)። ዓመቱ ትክክል ከሆነ ከቀኑ በታች ያለው ሮዝ ወይም ወርቅማ አረንጓድ ቁጥር፣ ተመሳሳይ ቀለም ያልውን ወርና የኢትዮጵያን ዓመት ከሁለተኛው የወር ክፍል በመውሰድ አቻውን ያገኛሉ፡፡ ለምሳሌ፦ 30/01/1945 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥር 22 1937 ይሆናል።
- ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ አቆጣጠር ለመቀየር ካሉበት ቀን መቁጠሪያ ላይ ሆነው ወሩንና ቀኑን (የኢትዮጵያን) ያግኙ። በኢትዮጵያው ዓመት ላይ 8 ይጨምሩ(ደምሩ)። ያለውን ዓመተምህረቱ በማጥፋት ያገኙትን ድምር ይክተቡና ያስኪዱት። ዓምቱን “፟-” “+” በመጫን ያስተካክሉ(ማሳሰቢያውን አይርሱ)። ከላይ በነጭ የተክተብው ቀን፣ በአንደኛው የወር ክፍል የሚገኘው ወርና ዓመት በመውሰድ አቻውን ያገኛሉ፡፡
- ለምሳል፦ ጳጉሜ 3 1962 ዓም የተወለድ በአውሮፓ አቆጣጠር Sep. 8, 1970 ይሆናል።
- አስረኛው የወር መደብ የሚይዝው የህዝብ በዓላትን ነው። የሙስሊም በዓል የሚውልበት ቀን ግምታዊ በመሆኑ የአንድና የሁለት ቀን ልዩነት ሊኖር ይችላል።